This site uses cookies to store information on your computer. I'm fine with this Cookie information

የእርግዝና መከላከያ ዘዴ

Different Types of Contraception - Amharic

ለምን አስፈላጊ ሆነ? 

የእርግዝና መከላከያ ዘዴ ያልተፈለገ እርግዝናን ለመከላከል ይጠቅማል የእርግዝና መከላከያ አገልግሎት UK ውስጥ ላሉ ብዙ ሰዎች በነጻ ይሰጣል። ሰ የአማራጭ ዓይነት ስላለ ለእርስዎ በተሻለ ሁኔታ ምቹ የሆነውን መምረጥ ይችላሉ።  

የእርግዝና መከላከያ ዘዴ አማራጮች 

መጀመሪያ የሚከተሉትን ለረጅም-ጊዜ የሚሰሩ እና ሊቀለበሱ የሚችሉትን እናያለን  

የሚተከል የእርግዝና መከላከያ 

የሆርሞን ማህጸን-ውስጥ የሚቀመጥ (Hormonal intrauterine system) (IUS) - ሆርሞን ያለው ጥቅልል 

የኮፐር ማህጸን-ውስጥ የሚቀመጥ መሳሪያ (Copper intrauterine device (IUD) - ‘ሆርሞን-የሌለው ጥቅልል 

 

በመርፌ የሚሰጥ የእርግዝና መከላከያ 

እነዚህን ዘዴዎች የሚጠቀሙ ሴቶች ሌሎች ዘዴዎችን ከሚጠቀሙ ሴቶች ይልቅ ያልታቀደ እርግዝና ሊያጋጥማቸው የሚችልበት እድል በጣም ዝቅተኛ እንእሆነ ይታወቃል 

ከዚህ በኋላ ተጨማሪ ልጆችን በጭራሽ እንደማይፈልጉ እርግጠኛ ከሆኑ እንግዲያውስ ማምከን ሥራ እንዲሰራልዎት ሊያስቡ ይችላሉ  

ሌሎች ሰፊ የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎች አሉ እነዚህም ውጤታማ ናቸው ግን እርግዝናን ለመከላከል በትክክል መጠቀም ያስፈልጋል 

 

ፕሮጄስቶጂን-ብቻ (1 ሆርሞን) እንክብል 

የተዋሀደ የሆርሞን የእርግዝና መከላከያ (2 ሆርሞኖች) 

እንክብል 

ቆዳ ላይ የሚለጠፍ 

ቀለበት 

ኮንዶሞች- እነዚህ በተጨማሪም በግብረ-ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች ስርጭትን መከላከል ይችላሉ ነገር ግን እነዚህ እንደ እርግዝና መከላከያ ዘዴ ከ100 ሴቶች በ18 ሴቶች ውስጥ ሳይሳኩ ሊቀሩ ይችላሉ 

ስለ እያንዳንዱ ዘዴ ዘርዘር ያለ መረጃ  

 

የሚተከል የእርግዝና መከላከያ (ተከላ) 

ተከላ ማለት ጥቃቅን ዘንግ የሚመስል ሆኖ የክብሪት እንጨት የሚያክል በክንድዎ ወደ ላይ በቆዳ ውስጥ የሚቀበር ነው  

የሚተከል የእርግዝና መከላከያው ኦቫሪ እንቁላል እንዳይለቁ የሚከላከል እና በሴርቪክስ (የማህጸን ጫፍ) ውስጥ ንፍጥ የሚመስል ፈሳሽን የሚያወፍር ፕሮጄስቶጂን የሚባል ሆርሞን ይለቃል ይህ በመጀመሪያ የወንድ የዘር-ፈሳሽ እንቁላል ጋር እንዳይደርስ መንገድ ለመዝጋት ይረዳል  

ጥቅሞች 

  • ለሦስት ዓመታ ይቆያል  
  • ከ10,000 ሴቶች 5 ብቻ ሳይሳካ ይቀራል 
  • ሲወጣ በፍጥነት ወደ መራባት አቅም መመለስ ይቻላል  
  • ቀላል ያሉ የወር አበባዎች እንዲኖሩ ሊያደርግ ይችላል 
  • ጡት ለያጠቡ ሴቶች ተመራጭ ነው 
  • አንዴ ካስገቡ መነካካት አያስፈልገውም እዚያው መተው ነው  

ጉዳቶች 

ሊያጋጥም የሚችሉ የተዛቡ የወር አበባዎች (ወይም ምንም የወር አበባ አለመታየት) 

ሆርሞን ያለው የማህጸን-ውስጥ ሲስተም (IUS) 

የሆርሞን IUS ትንሽ  T ቅርጽ ያለው መሳሪያ ሆኖ በማህጸንዎ ውስጥ የሚቀመጥ ነው  

የማህጸን ዙሪያን ቀጭን (ይህ በወር አበባ ወቅት የሚደማ አካል ነው) አድርጎ በማቆየት እርግዝናን ይከላከላል እናም ለዚህ ምክንያት ሴቶች ብዙውን ጊዜ ቀላል የወር አበባዎች ይኖራቸዋል ወይም ምንም የወር አበባ አያዩም።  

እንዲሁም በሴርቪክስ (የማህጸን ጫፍ) ውስጥ ንፍጥ የሚመስል ፈሳሽን ያወፍራል ይህ ደግሞ መጀመሪያ ላይ የወንድ የዘር-ፈሳሽ ወደ እንቁላሉ ጋር እንዳይደርስ መንገድ ለመዝጋት ይረዳል 

ጥቅሞች 

  • እስከ አምስት ዓመታት ሊቆይ ይችላል 
  • ከ1000 ሴቶች በ2 ውስጥ ብቻ ሳይሳካ ይቀራል 
  • አንዴ ካስገቡ እዚያው መተው ነው (መነካካት አያስፈልገውም) 
  • አስፈላጊ ሲሆን በቀላሉ ሊወጣ ይችላል 
  • በጣም ዝቅተኛ ዶዝ ደህንነት ያለው ሆርሞን ነው 
  • ሲወጣ በፍጥነት ወደ መራባት አቅም መመለስ ይቻላል  
  • የወር አበባዎች/የደም መፍሰስ ምናልባት ቀላል ይሆናሉ (ወይም መድማት ሙሉ በሙሉ ሊቆም ይችላል)። ይህ ለጤና ጥሩ ነው በተለይ አንድ ሴት ከባድ ለረጂም-ጊዜ የሚቆይ ወይም ህመም ያላቸው የወር አበባዎች ከነበሯት።  
  • ጡት ለሚያጠቡ ሴቶች አመቺ ነው 

ጉዳቶች 

  • ዝቅተኛ ኢንፌክሽን ተጋላጭነት 
  • ለመቆም የተወሰኑ ወራትን ሊወስድ የሚችል የተዛባ ደም መፍሰስ  

የኮፐር የማህጸን-ውስጥ መሳሪያ (IUD) - ‘ሆርሞን-የሌለው ጥቅልል’ 

የኮፐር IUD ትንሽ  T ቅርጽ ያለው መሳሪያ ሆኖ በማህጸንዎ ውስጥ የሚቀመጥ እና የወንድ የዘር-ፈሳሽ የሚንቀሳቀስበትን መንገድ የሚቀይር ነው 

ይህ ደግሞ እንቁላልን ከማዳበር ይከለላል ይህ IUD ዓይነት ትንሽ መጠን ተፈጥሮአዊ እና አደጋ የሌለው ኮፐር አለው። 100% ከሆርሞን ነጻ ሆኖ የወር አበባ በመደበኛ ጊዜ እንዲመጣ ያደርጋል  

ጥቅሞች 

  • ከ5 እስከ 10 ዓመታት ይቆያል (የኮፐር IUD ዓይነት ላይ በመመርኮዝ) 
  • 1000 ሴቶች 8 ብቻ ሳይሳካ ይቀራል 
  • አስፈላጊ ሲሆን በቀላሉ ሊወጣ ይችላል 
  • ከሆርሞን  ነው 
  • አንዴ ካስገቡ መነካካት አያስፈልገውም እዚያው መተው ነው  
  • መደበኛ የወር አበባዎን አይለውጥም 
  • ሲወጣ በፍጥነት ወደ መራባት አቅም መመለስ ይቻላል  
  • ጡት ለሚያጠቡ ሴቶች ተመራጭ ነው 

ጉዳቶች 

  • ዝቅተኛ ኢንፌክሽን ተጋላጭነት 
  • የወር አበባዎ ብዙ/ረዘም ያሉ ሊሆኑ ይችላሉ እና  የሚሆን ከሆነ ደግሞ የበለጠ የህመም ስሜትን ፈጥር ይችላ 

 በመርፌ የሚሰጥ የእርግዝና መከላከያ 

ጃጉ የሚመስለውን ነው ከማርገዝ የሚያቆምዎ መርፌ ነው ጃጉ ፕሮጄስቶጂን አለው ኦቫሪዎችዎ እንቁላሎችን እንዳይለቁ የሚከላከል ሆርሞን እንዲሁም በሴርቪክስ (የማህጸን ጫፍ) ውስጥ ንፍጥ የሚመስል ፈሳሽን ያወፍራል መጀመሪያ ላይ የወንድ የዘር ፍሬ ወደ እንቁላል እንዳይደርስ መንገድ ለመግዛት የሚረዳ።  

ጥቅሞች 

  • ለ3 ወራት ይቆያል 
  • 100 ሴቶች 6 ውስጥ ሳይሳካ ይቀራል 
  • ቀለል ያሉ የወር አበባዎች ወይም ምንም የወር አበባ ላይታይ ይችላል 
  • ጡት ለሚያጠቡ ሴቶች አመቺ ነው 
  • እንዲሁም በነርስ ወይ በሀኪም ሚሰጥ የተወሰነ ስልጠና በኋላ በየ 3 ወራት እራስዎን በራስዎ የሚ አዲስ መርፌ አለ 

ጉዳቶች 

  • ለመርፌው በእየ ሶስት ወራት የጤና ባለሙያን ማየት አለብዎት (በእራስዎ መወጋት የሚችሉትን መርፌ ከመረጡ በስተቀር 
  • መርፌውን መጠቀም ሲያቆሙ ወደ መራቢያ አቅም ለመመለስ የመዘግየት እድል አለው 
  • ሊያጋጥሙ የሚችሉ የተዛቡ የወር አበባዎች 

የፕሮጄስቶጂን ብቻ ክኒን (POP) 

እነዚህ ክኒኖች አንድ ሆርሞን ፕሮጄስቶጂን ብቻ አላቸው ክኒኖች በየቀኑ ይወሰዳሉ ሁለት ዓይነት ፕሮጄስቶጂን ብቻ ክኒን አሉ የማህጸን ጫፍ ፈሳሽን የሚያወፍር እና የወንድ የዘር ፍሬ እንቁላል ጋር እንዳይደርስ የሚያቆም ነባሩ ዓይነት እና ኦቫሪዎች እንቁላል እንዳይለቁ የሚያቆም አዲሱ POP ዓይነት  

ጥቅሞች 

  • 100 ሴቶች 9 ውስጥ ሳይሳካ ይቀራል 
  • ከማቆም በኋላ የሚቀለበስ ነው 
  • ጡት ለሚያጠቡ ሴቶች አመቺ ነው 
  • ኤስትሮጂን ሆርሞን መውሰድ ለማይችሉ ሴቶች ደህንነት አለው  
  • የደም መፍሰስ ላይኖር ይችላል 

ጉዳቶች 

  • የተዛባ የደም መፍሰስ/የወር-አበባ ሊኖረው ይችላል 
  • በየቀኑ በተመሳሳይ ቀን ለመውሰድ ማስታወስ ያስፈልጋል  
  • ተቅማጥ ወይም ወደ ላይ የማስመለስ ሁኔታ ካለ ላይሰራ ይችላል 

የተዋሀደ የሆርሞን የእርግዝና መከላከያ (CHC) 

እነዚህ ዘዴዎች ሁለት ሆርሞኖች አሉት ኤስትሮጂን እና ፕሮጄስቶጂን 

ኦቫሪዎችዎ እንቁላል እንዳይለቁ ይከላከላሉ 

ብዙውን ጊዜ ይህ በየቀኑ በተመሳሳይ ጊዜ የሚወስዱት ክኒን ነው 

በገበያ ላይ ብዙ የተለያዩ ዓይነቶች ክኒኖች አሉ 

እንዲሁም እንደ ክኒኑ የሚሰሩ የቆዳ ላይ መለጠፊያዎች ወይም የሴት ብሊት ውስጥ የሚደረጉ ቀለበቶች አሉ 

ጥቅሞች 

  • 100 ሴቶች 9 ውስጥ ሳይሳካ ይቀራል 
  • ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ቀለል ያለ እና ዝቅተኛ ህመም ያለው የወር አበባ 
  • ከማቆም በኋላ የሚቀለበስ ነው 
  • ለብጉር ሊጠቅም ይችላል 
  • ጡት ለሚያጠቡ ሴቶች አመቺ ነው 

 ጉዳቶች 

  • ይህን ዘዴ የሚጠቀሙ የተወሰኑ ሴቶች ከፍተኛ የደም ግፊት ወይም በእግሮች ወይም ሳምባዎች ውስጥ የደም መርጋት ሊያጋጥማቸው ይችላል ይህ በጣም ዝቅተኛ ስጋት ነው በዚህ ምክንያት የተወሰኑ ቅድሚያ የነበሩ የጤና ጉዳዮች ካሉዎት CHC ለመጠቀም ላይችሉ ይችላሉ 
  • ዘዴውን በትክክል መጠቀም ያስፈልጋል 
  • ተቅማጥ ወይም ወደ ላይ የማስመለስ ሁኔታ ካለ ላይሰራ ይችላል 

የሴት ማምከን 

ይህ የወንድ የዘር ፍሬ እንቁላል ለማግኘት እንዳይተላለፍ የፋሎፒያን ቱቦን መዝጋትን ያካትታል 

በዚህ በራሪ ወረቀት ውስጥ የተጠቀሱ የማህጸን-ውስጥ ዘዴዎች (የሆርሞን IUS እና የኮፐር IUD) እና የተከላ ዘዴ ከሴት ማምከን የበለጡ ውጤታማ ናቸው 

ጥቅሞች 

  • ዘላዊ ነው 
  • 200 ሴቶች 1 ውስጥ ሳይሳካ ይቀራል 
  • የወር አበባዎች ላይ ለውጥ አይመጣም 

 ጉዳቶች 

  • የሚቀለበስ አይደለም 
  • ሌላ እርግዝና በጭራሽ እንደማይፈልጉ እርግጠኛ መሆን አለብዎት 
  • የቀዶ-ጥገና አሰራር ያስፈልጋል  
  • የጠቅላላ ማደንዛዣ መድሃኒት ሊያስፈልግ ይችላል 

የወንድ ማምከን - ቫዜክቶሚ 

ይህ የወንድ የዘር ፍሬን ከቴስቲክሎች ወደ ወንድ ብሊት የሚወስዱ ቱቦች (ቫስ ዲፌሬንስ) መዝጋትን ያካትታል እርሱም በጠቅላላ ማደንዘዣ ስር የሚደረግ ፈጣን አሰራር ነው በማህበረሰብ ክሊኒክ ውስጥ መደረግ ይችላል 

ለአካባቢ አገልግሎቶች እባክዎ የበራሪ ወረቀቱን የመጨረሻ ገጽ ይመልከቱ 

የወንድ ማምከን ከሴት ማምከን የበለጠ ውጤታማ እና በጣም ቀላል አሰራር ነው 

ጥቅሞች 

  • ዘላዊ ነው 
  • 2000 ሴቶች 1 ውስጥ ሳይሳካ ይቀራል 
  • የአካባቢ የማደንዘዣ መድሃኒት በመጠቀም ይደረጋል 

ጉዳቶች 

  • የሚቀለበስ አይደለም 
  • የቀዶ-ጥገና አሰራር ያስፈልጋል  
  • ውስብስብ ችግር የማስከተል ስጋት አለው 
  • አሰራሩ የተሳካ መሆኑ እስኪረጋገጥ ድረስ አስተማማኝ የሆነ የእርግዝና መከላከያን መጠቀም ያስፈልጋል ይህ ከአሰራሩ በኋላ በ12 ሳምንታት ይደረጋል 

የቫዜክቶሚ አገልግሎት 

በሳንዲፎርድ የወሲባዊ ጤና አገልግሎት መሰረት 

ቀጠሮዎች የሚከተለውን በማድረግ ይያዛል፡  

ለቫሴክቶሚ ቅድመ-ቀዶጥገና ቀጠሮ ራስን ሪፌር ማድረግ (0141 211 8654)  

የድንገተኛ ጊዜ የወሊድ መከላከያ 

ሁለት የድንገተኛ ጊዜ የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎች አሉ - የኮፐር IUD (ጥቅልል) እና የሆርሞን እንክብሎች  

የኮፐር የማህጸን-ውስጥ መሳሪያ (IUD) - ‘ሆርሞን-የሌለው ጥቅልል’  

ይህ በጣም ውጤታማ የድንገተኛ ጊዜ የእርግዝና መከላከያ ነው (99% ውጤታማ ነው) እና ከድንገተኛ ጊዜ የሆርሞን እንክብሎች ይልቅ 10 ጊዜ ውጤታማ ነው 

የድንገተኛ ጊዜ IUD ልቅ የግብ-ስጋ ግንኙነት በኋላ እስከ 5 ቀ ውስጥ (አንዳንድ ጊዜ ሊበልጥም ይችላል) በወር አበባዎ ዙር ውስጥ ብዙ ጊዜ እንዲገባልዎ ሊያደርጉ ይችላሉ  

አብዛኛውን ጊዜ ለማስገባት ቀላል ነው እና በማንኛውም እድሜ ላይ ላሉ ሴቶች አመቺ ነው ለድንገተኛ ጊዜ የእርግዝና መከላከያ ቢያንስ እስከሚቀጥለው የወር አበባዎ በማህጸንዎ ውስጥ መቆየት አለበት ነገር ግን እንደ ዋና የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎ ለማቆየት ሊወስኑ ይችላሉ 

የፕሮጄስቶጂን እንክብል (ለምሳሌ Levonelle TM) 

ከልቅ የግብረስጋ ግንነት በኋላ በ24 ሰዓታት ውስጥ ከተወሰደ በጣም ውጤታማ ይሆናል የእንቁላል መለቀቅን በማዘግየት ይሰራል (ስለዚህ ይህ አስቀድሞውኑ ተደርጎ ከሆነ እንክብሉ ውጤታማ አይሆንም)።  

ከልቅ የግብረስጋ ግንኙነት በኋላ እስከ 3 ቀናት ሊወሰድ ይችላል ግን ሳይውስዱ በዘገዩ ቁጥር ውጤታማነቱ እያነሰ ይሄዳል።  

ይህንን እንክብል GP ተመዝግበው ከሆነ በስኮትላንድ ውስጥ ካሉ ፋርማሲዎች  ወይም አካባቢዎ በሚገኝ የወሲባዊ ጤና ክሊኒክ ማግኘት ይችላሉ 

ዩሊፕሪስታል አሴቴት (ለምሳሌ EllaOne TM) 

ይህ እንክብል ልቅ የግብረስጋ ግንኙነት በኋላ እስከ 5 ቀናት ውስጥ መወሰድ ይችላል እሱም የእንቁላል ዳበርን በማዘግየት ይሰራል (ስለዚህ ይህ አስቀድሞውኑ ተደርጎ ከሆነ እንክብሉ ውጤታማ አይሆንም)።  

እንክብሉ ከፕሮጄስቶጂን የድንገተኛ ጊዜ የእርግዝና መከላከያ የበለጠ ውጤታማ ነው።  

EllaOne TM GP ተመዝግ ከሆነ በስኮትላንድ ውስጥ ካሉ ፋርማሲዎች ወይም ከአካባቢዎ የወሲባዊ ጤና ክሊኒክ በነጻ ማግኘት ይችላሉ 

ሆርሞን ያላቸው የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎች EllaOne TM ውጤታማነትን ይቀንሳ፣ ስለዚህ EllaOne TMን ከወሰዱ በኋላ ማንኛውም ሆርሞን ያላቸው የእርግዝና መከላከያ ዘዴዎችን ለ5 ቀናት መጠቀም የለብዎትም። 

ጡት የሚያጠቡ ሴቶች EllaOne TMን ከወሰዱ በኋላ ለ7 ቀናት የጡት ወተትን እንዲያፍስሱ እና ልጃቸውን እንዳያጠቡ ይመከራል።  

GP ልምምዶች የእርግዝና መከላከያን ማቅረብ ይችላሉ። በሚሄዱት የልምምድዎ ቦታ ምን እንዳለ ለማወቅ መጠየቅ ጠቃሚ ነው።  

የሳንዲፎርድ (Sandyford) ወሲባዊ ጤና አገልግሎት  

ሙሉ የወሲባዊ ጤና አገልግሎትን ይሰጣል የሚከተሉትን ጨምሮ 

  • የእርግዝና መከላከያ ዘዴ መረጃ እና አቅርቦት  
  • የማህጸን-ውስጥ የእርግዝና መከላከያ ጥቅልል ማስገባት እና ማውጣት  
  • የሚተከል የእርግዝና መከላከያን ማስገባት እና ማውጣት 
  • ቫዜክቶሚ (ቀዶ ህክምና) 
  • ይፅንስ ማቋረጥ ወይም ውርጃ አገልግሎቶች  

ለቀጠሮ መረጃ እና ምክር አገልግሎት  0141 211 8130 ይደውሉ ስልኮቻችን ከሰኞ እስከ አርብ 230- 1015  የበዓል ቀናት ሳይጨምር ወይም https://www.sandyford.scot ይጎብኙ 

የኢንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪ ካልሆኑ በቀጠሮዎ ላይ አስተርጓሚ እንዲቀርብልዎ መጠየቅ ይችላሉ ቀጠሮዎን ሲይዙ የሚፈልጉትን ቋንቋ እና የአነጋገር ዘዬን ይንገሩን እናመቻችልዎታለን ተጨማሪ መረጃ  https://www.sandyford.scot/interpreter ያገኙ ይችላ