የድንገተኛ ጊዜ እርግዝና መከላከያ
ያለ እርግዝና መከላከያ ዘዴ ወሲባዊ ግንኙነት አድርገው ከሆነ፣ ወይም የእርግዝና መከላከያው ካልተሳካ፣ የድንገተኛ ጊዜ የእርግዝና መከላከያ የማርገዝ እድሎችን ይቀንሳል። 2 ዓይነቶች አሉ፡
የድንገተኛ ጊዜ እርግዝና መከላከያ ክኒን ከወሲብ በኋላ እስከ 5 ቀናት ሊወሰዱ ይችላሉ። ከወሲብ በኋላ በፍጥነት በተወሰደ እና በወር አበባዎ የመጀመሪያ አካባቢ በተወሰደ ቁጥር፣ የበለጠ ውጤታማ ይሆናል። የድንገተኛ ጊዜ እርግዝና መከላከያ ክኒን ከብዙ ፋርማሲዎች፣ GPዎች እንዲሁም ከሳንዲፎርድ ይገኛል።
IUD በጣም ውጤታማ የሆነ የድንገተኛ ጊዜ የእርግዛና መከላከያ ነው። እርሱም ከ99% በላይ ውጤታማ ነው እና ከሚቀጥለው ወር አበባዎ በኋላ ለማቆየትም ሆነ ለማስወጣት መምረጥ ይችላሉ። ጥበቃ ያልተደረገለት ወሲብ ከፈጸሙ በኋላ በአምስት ቀናት ውስጥ፣ ወይም፣ እርስዎ እንቁላል የሚለቁበት (ኦቩሌት) ቀን ለመገመት ከተቻለ፣ ከኦቩሌሽን በኋላ እስከ አምስት ቀናት ውስጥ፣ በጤና እንክብካቤ ባለሙያ መግባት አለበት።
ቀጠሮ እንዴት ይያዛል?
ቀጠሮ ለመያዝ በ 0141 211 8130 ለሳንዲፎርድ ይደውሉ።
የኢንግሊዝኛ ቋንቋ ተናጋሪ ካልሆኑ፣ በቀጠሮዎ ላይ አስተርጓሚ እንዲቀርብልዎ መጠየቅ ይችላሉ። ቀጠሮዎን ሲይዙ የሚፈልጉትን ቋንቋ ይንገሩን እና እናመቻችልዎታለን።
የአስተርጓሚ አገልግሎት በተመለከተ ተጨማሪ መረጃ በ https://www.sandyford.scot/sexual-health-services/i-need-an-interpreter/ ይገኛል።
https://nashonlinebooking.com/onlinebookingsystem/en/?hbref=7303069
ሚስጥራዊነት
በሚስጥር የሚያዝ አገልግሎት እንሰጣለን እና ያለ እርስዎ ፈቃድ እርስዎን የሚመለከት መለየት የሚችል መረጃን ለማንኛውም ሰው አናጋራም፣ እርስዎ ወይም ሌላ ሰው አደጋ ውስጥ እንዳላችሁ ወይም ጤና ላይ አደጋ እንዳለ ካመንን በስተቀር። ሲመጡ እውነተኛ ስምዎን እንዲጠቀሙ እናበረታታዎታለን እና በሳንዲፎርድ ውስጥ በኤሌክትሮኒክ መዝገባችን ላይ በደህንነት ይያዛል።
ስለ ወሲባዊ ጤናዎ ከእኛ ጋር መነጋገር
በጉብኝትዎ ወቅት በጣም ጥሩ እንክብካቤ እንደሚያገኙ ለማረጋገጥ፣ የሳንዲፎርድ ሠራተኛ ስለ ህክምና እና ወሲባዊ ታርክዎ ግላዊ እና ጥንቃቄ የሚሹ ጥያቄዎችን ሊጠይቁ ይችላሉ፣ ለመጨረሻ ጊዜ ወሲባዊ ግንኙነት መቼ እንዳደረጉ፣ ጥበቃ ያልተደረገለት ወሲብ አድርገው እንደሆነ እና ማንኛውም የበሽታ ምልክቶች ያሉብዎት እንደሆነ የመሳሰሉትን ዓይነት።
ሠራተኞች እርስዎን ለመወቀስ እዚያ አልተገኙም። ማንኛውም እርስዎ የምናገሩት ነገር አያደነግጠንም ወይም እፍረት አያሰማንም፣ ነገር ግን በተሻለ ሁኔታ እርስዎን መመርመር፣ ማከም እና መደገፍ እንድንችል ሀቁን መናገር ይኖርብዎታል። የምትናገሩት ሁሉም ነገር በኤሌክትሮኒክ መዝገብ ሥርዓታችን ላይ በሚስጥር ይያዛል፣ ወደ ሌላ አገልግሎት እርስዎን ለመላክ፣ በእርስዎ ፈቃድ፣ መረጃ ማጋራት ካስፈለገን በስተቀር። በጣም አልፈው አልፈው በሚታዩ ሁኔታዎች ውስጥ፣ ሠራተኞች ለእርስዎ ጥበቃ ሲባል መረጃ ማጋራት ሊያስገልጋቸው ይችላል።
የሚመርጡ ከሆነ፣ ወንድ ወይም ሴት የጤና ባለሙያን ለማየት መምረጥ ይችላሉ፣ ነገር ግን ክሊኒኩ ሥራ የሚበዛበት ከሆነ ከተለመደው በላይ ረጅም ጊዜ መጠበቅ ሊኖርብዎት ይችላል፣ እና ቀጠሮዎን ሲይዙ ይህንን ሊያሳውቁን ይገባል።
ከመምጣትዎ በፊት ምን ይጠበቃሉ?
የቀጠሮ ርዝመቶች ከ10 ደቂቃዎች እስከ 90 ደቂቃዎች ሊለያዩ ይችላሉ። በቀጠሮዎ ላይ ለፍላጎቶችዎ እንደምንጨቅ ለማረጋገጥ የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን፣ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ፣ እንደምንሰጠው የአገልግሎት አካል፣ ለሌላ ቀጠሮ ተመልሰው እንዲመጡ ልንጠይቅዎት እንችላለን።
ከቀጠሮዎ በፊት ደብዳቤ ከላክንልዎት የሚፈልጉትን ሁሉም ተገቢ የቅድመ-ቀጠሮ መረጃን እናካትታለን።
ቀጠሮ ላይ ሲገኙ ምን ይጠብቃሉ?
ለአስተርጓሚ ጠይቀው ከሆነ፣ በቀጠሮዎ ጊዜ ያገኙዎታል።
እኔ ሲደርስ ምን ይፈጠራል?
ሲደርሱ፣ የቁጥር ካርድ፣ የሚቀርበው አገልግሎት ላይ መረጃ ያካተተ ጥቅል፣ የግል መረጃዎ ምን እንደሚሆን የሚያብራራ የሚስጥራዊነት ሰነድ፣ እና የምዝገባ ቅጽ በሚሰጥዎ/በምትሰጥዎ እንግዳ ተቀባይ ይቀበላሉ። የእንግዳ ተቀባዩ/ዋ ለመመዝገብ ተራዎ እስኪደርስ ድረስ እንዲቀመጡ ይጠይቅዎታል/ትጠይቅዎታለች። የምዝገባ ቅጽ መሙላት ላይ እርዳታ የሚፈልጉ ከሆነ ለእንግዳይ ተቀባይ ማሳወቅ ይችላሉ። እባክዎ ይህንን በቻሉት መጠን ይሙሉ።
ለምን ያህል ጊዜ መጠበቅ አለብኝ?
በተሰጠዎት የቀጠሮ ጊዜ ተቀራራቢ ላይ እንዲታዩ የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን። እንዳለመታደል ሆኖ፣ ያ ሳይሆን የሚቀርባቸው ሁኔታዎች አሉ። ለቀጠሮ መጥተው ለ30 ደቂቃዎች ጠብቀው እና ካልተጠሩ፣ እባክዎ ለእርስዎ ምን እየተደረገ እንደሆነ መጠየቅ ለሚችል/ለምትችል የእንግዳ መቀበያ አባል ያሳውቁ። በአንድ ጊዜ የሚሰሩ ብዙ ክሊኒኮች ስላሉን፣ ከእርስዎ ኋላ የደረሰ ሰው በኋላ ሊጠሩ ይችላሉ።
ዘግይቼ ከደረስኩስ?
ታካሚዎች ለቀጠሯቸው ዘግይተው የሚደርሱባቸው አጋጣሚዎች እንዳሉ እናውቃለን። ለቀጠሮዎ ዘግይተው ከደረሱ፣ ሙሉ የመጀመሪያው የቀጠሮዎ ጊዜን ማክበር እንደምንችል ዋስትና መስጠት አንችልም። ለቀጠሮዎ ዘግይተው ሲደርሱ፣ የክሊኒክ ቡድን አባል መጥቶ/ታ እንዲያናግርዎ/እንድታናግርዎ እንግዳ ተቀባዩ/ዋ ያመቻቻል/ታመቻቻለች። አንድ ሰው እስኪገኝ ድረስ መጠበቅ ሊኖርብዎት ይችላል። ለአንዳንድ ክሊኒኮች እና አሰራሮች ከዘገዩ እርስዎን ለማየት አንችልም። ይህ የሚሆን ከሆነ፣ አማራጭ ቀጠሮን እናመቻችልዎታለን።
በማማከሪያው ጊዜ ማንን አገኛለሁ?
ብዙ አገልግሎቶቻችን የክሊኒካል ባለሙያዎች ቡድን ሠራተኞች አላቸው፣ በአገልግሎቱ መሰረት፣ ሀኪሞች፣ ነርሶች፣ የጤና እንክብካቤ እርዳታ ሰጪዎች፣ አማካሪዎች ወይም የስነ-ልቦና ባለሙያዎች ሊሆኑ የምችሉትን። ሁሉም ሠራተኞቻችን፣ እርስዎ ወደ ክሊኒክ ክፍል ሲጠሩ፣ እራሳቸውብ ያስተዋውቃሉ።
ለተለየ የክሊኒክ/የህክምና ባለሙያ ጾታ ምርጫ ካለዎት፣ እባክዎ ቀጠሮዎን ሲይዙ ያሳውቁን። ስንችል ያንን ጥያቄ ለማክበር እንሞክራለን ነገር ግን ዋስትና መስጠት አንችልም።
ምርመራዎቼ እንዴት ይወሰዳሉ?
በግብረ-ስጋ ግንኙነት ለሚተላለፉ አባላዘር በሽታዎች ምርምራ ከፈለጉ ወይም ማድረግ ከለብዎት፣ የሽንት ወይም የደም ናሙና ማቅረብ ሊኖርብዎት ይችላል። አንዳንድ ምርመራዎች ከመራቢያ ብልቶችዎ የፈሳሽ ጥርግ እንዲወሰድ ሊያስፈልጉ ይችላሉ እና፣ ምን ዓይነት ወሲብ እንደፈጸሙ ላይ በመመርኮዝ፣ ከጉሮሮዎ እና ከትልቁ አንጀት ጫፍ (ፈንጢጣ) ሊወሰድ ይችላል። ይህ ትንሽ ምቹ ላይሆን ይችላል፣ ነገር ግን የክሊኒክ ሠራተኞች እነዚህን ምርመራዎች ለማድረግ የላቀ ስልጠና አላቸው እና በጥሩ እጆች ውስጥ ነው ያሉት። አንዳንድ ምርመራዎች ሀኪሙ/ሟ ብልቶችዎን እንዲያይ/እንድታይ ሊያስፈልጉ ይችላሉ። ተመሳሳይ ጾታ ባለው/ላት ሀኪም መታየት የተሻለ ምቾት የሚሰጥዎ ከሆነ፣ እባክዎ ቀጠሮዎን ሲይይዙ ያሳውቁን።
ልጆችን ይዤ መምጣት እችላለሁ?
ልጆችን ይዞ አለመምጣት በጣም ጥሩ ነው እናም በህንጻው ላይ የልጅ እንክብካቤ አገልግሎቶች የሉም። ከልጅዎ ጋር መምጣት ካለብዎት፣ እርስዎ በክሊኒክ ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ በመጠባበቂያ አካባቢ ውስጥ የሚያንከባክቧቸውን ሌላ አዋቂ ይዘው ኑ። ልጆችዎን ከሚታመን አዋቂ ሰው ጋር መተው ከቻሉ በርካታ የመጫወቻ አካባቢ ያለው ተወዳጅ ፓርክ በመንገዱ አልፎ አለ። ካልሆነ፣ ልጆችዎን ትተው ሌላ ጊዜ ተመልሰው እንዲመጡ ሊጠየቁ ይችላሉ።