Testing - Amharic
ምርመራ
ለSTI (በግብረ-ስጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች) መመርመር ለምን ያስፈልጋል?
በSTI ምክንያት ሊመጡ የሚችሉ ማንኛውም ምልክቶች ካሉዎት እንዲሁም ወሲባዊ ጓደኛ ቀይረው ከሆነ ወይም STI የነበረው/ራት ጓደኛ ካለዎት መመርመር አስፈላጊ ነው። ብዙውን ጊዜ STI ያለባቸው ሰዎች ምልክቶችን አያሳዩም፣ ስለዚህ በበሽታዎች የመያዝ አደጋ ከነበረዎት እና በቅርብ ጊዜ ተመርምረው የማያውቁ ከሆነ መመርመር ሁል ጊዜ ዋጋ አለው።
የተለመዱ የSTI ምልክቶች
- ሽንት ሲተላለፍ (ሲሸኑ) የህመም ስሜት
- በመራቢያ ብልቶች አካባቢ የማሳከክ፣ የማቃጠል ወይም መጠነኛ የመዋጋት ስሜት
- ከመራቢያ ብልቶች ወይም ፊንጢጣ የሚወጣ አዲስ ፈሳሽ
- የመራቢያ ብልቶች ወይም ፊንጢጣ አካባቢ ውሃ የቋጠሩ ብጉሮች፣ ቁስሎች፣ ነጠብጣቦች ወይም እብጠቶች
- በወር-አበባዎች መካከል ወይም ከወሲብ በኋላ የሚፈጠር መድማት
- በወሲብ ጊዜ የሚሰማ ህመም
- የዝቅተኛ አንጀት አካባቢ ህመም
- ጉንፋን የሚመስሉ ምልክቶች ጋር የሚታዩ በሰውነት ላይ የሚታዩ ሽፍታዎች
መቼ ነው ምርመራ የሚደረገው
ምልክቶች ከታዩብዎት ወይም በሽታዎች ካለባቸው ሰዎች ጋር ግንኙነት አድርገው ከሆነ፣ በተቻለ ፍጥነት መታየት አስፈላጊ ነው። ቀጠሮ ለመያዝ እባክዎ በ 0141 211 8130 ይደውሉልን።
ምልክቶች ከሌሉብዎት አንዳንድ ጊዜ መጠበቅ የተሻለ ሊሆን ይችላል፣ ምክንያቱም ምርመራዎቻችን መኖራቸውን እንዲያገኙ ሰውነትዎ የበሽታ ምልክቶችን ለማሳየት የተወሰነ ጊዜ መውሰድ ስለሚችል። ምርመራ ከመውሰድዎ በፊት እባክዎ ከታች ያለውን መረጃ ከግምት ውስጥ ያስገቡ። በጣም አስቀድሞ ከተደረገ ትክክል ላይሆን ይችላል።
- ክላሚዲያ እና ጨብጥ በምርመራ ላይ ለመገኘት፣ ከወሲብ በኋላ ሁለት ሳምንታትን ሊወስድ ይችላል።
- የ HIV ምርመራ ከወሲባዊ ግንኙነት በኋላ በ45 ቀናት (6 ሳምንታት አካባቢ) ከፍተኛ ትክክለኝነት አለው።
- ቂጥኝ ከወሲብ በኋላ ለመታየት እስከ 12 ሳምንታት መውሰድ ይችላል
ባለፉት 72 ሰዓታት ውስጥ ስለ HIV ተጋላጭነት አደጋ ሀሳብ ከገባዎ፣ እባክዎ በ 0141 211 8130 ይደውሉልን፣ በሽታን ለመከላከል ህክምና፣ PEP፣ ሊያስፈልግዎት ስለሚችል።
ቀጠሮ እንዴት ይያዛል?
በ 0141 211 8130 ለሳንዲፎርድ ይደውሉ። ኢንግሊዝኛ ተናጋሪ ካልሆኑ፣ በቀጠሮዎ ላይ አስተርጓሚ እንዲቀርብልዎ መጠየቅ ይችላሉ። ቀጠሮዎን ሲይዙ የሚፈልጉትን ቋንቋ እና የአነጋገር ዘዬ ይንገሩን እና እናመቻችልዎታለን።
በአስተርጓሚ አገልግሎት ዙሪያ ተጨማሪ መረጃ በ I Need an Interpreter for my Appointment (sandyford.scot) ሊገኝ ይችላል
ምርመራ እንዴት ይደረጋል?
መመርመር በእውነቱ ቀላል ነው። ለቀጠሮዎ ሲመጡ፣ ለእርስዎ ለማቅረብ ትክክለኛ ምርመራዎች የትኞቹ እንደሆኑ ማወቅ እንድንችል፣ ስለ አጠቃላይ ጤናዎ እና ወሲባዊ ህይወትዎ የተወሰኑ ጥያቄዎችን እርስዎን መጠየቅ ይኖርብናል። በአጠቃላይ ለሁሉም ሰው የክላሚዲያ፣ ጨብጥ፣ ቂጥኝ እና የHIV ምርመራዎች ይሰጣሉ። አንዳንድ ጊዜ ለተጨማሪ በሽታዎች ምርመራ እናደርጋለን፣ አስፈላጊ ከሆነ። ይህ በቀኑ ከእርስዎ ጋር ይነጋገርበታል።
HIV እና ቂጥኝ የደም ምርመራ በመውሰድ ምርመራ ይደረግላቸዋል። ክላሚዲያ እና ጨብጥ በሴቶች ውስጥ የሰውነት ፈሳሽ ናሙና እና በወንዶች ውስጥ ደግሞ የሽንት ናሙና እና፣ አስፈላጊ ሲሆን፣ የፈሳሽ ናሙናን ጭምር በመውሰድ ምርመራ ይደረግላቸዋል። ምልክቶች ከሌሉብዎ እነዚህን ናሙናዎች በራስዎ መውሰድ ይችላሉ።
ክላሚዲያ፣ ጨብጥ፣ ትሪኮሞናስ፣ የፔልቪክ ኢንፍላማቶሪ ዲዚዝ፣ ቂጥኝ፣ የመራቢያ ብልት ሄርፕስ፣ የመራቢያ ብልት ኪንታሮቶች፣ LGV፣ የሕዝብ ቅማል፣ ሽፍታ ላይ ተጨማሪ መረጃ በ NHS ማሳወቂያ ላይ ይገኛል - በእያንዳንዱ ደረ-ገጾች ላይ፣ በቀኝ-እጅ በኩላ ያለው አምድ ላይ ወደ ትርጉሞች የሚወስድ አገናኝ መስመር አለ፡
ሚስጥራዊነት
በሚስጥር የሚያዝ አገልግሎት እንሰጣለን እና ያለ እርስዎ ፈቃድ እርስዎን የሚመለከት መለየት የሚችል መረጃን ለማንኛውም ሰው አናጋራም፣ እንዲናደርግ በህግ ከተጠየቅን፣ ወይም እርስዎ ወይም ሌላ ሰው አደጋ ውስጥ እንዳላችሁ ወይም ጤና ላይ አደጋ እንዳለ ካመንን በስተቀር። ሲመጡ እውነተኛ ስምዎን እንዲጠቀሙ እናበረታታዎታለን እና በሳንዲፎርድ ውስጥ በኤሌክትሮኒክ መዝገባችን ላይ በሚስጥር ይያዛል።
ስለ ወሲባዊ ጤናዎ ከእኛ ጋር መነጋገር
በጉብኝትዎ ወቅት በጣም ጥሩ እንክብካቤ እንደሚያገኙ ለማረጋገጥ፣ የሳንዲፎርድ ሠራተኛ ስለ ህክምና እና ወሲባዊ ታርክዎ ግላዊ እና ጥንቃቄ የሚሹ ጥያቄዎችን ሊጠይቁ ይችላሉ፣ የሚከተሉትን ዓይነት፡
- ለመጨረሻ ጊዜ ወሲባዊ ግንኙነት መቼ እንዳደረጉ
- ጥበቃ ያልተደረገለት ወሲብ አድርገው እንደሆነ
- ማንኛውም ምልክቶች ያሉብዎት እንደሆነ
- በሽታ እንዳለዎት ለምን እንዳሰቡ
ሠራተኞች እርስዎን ለመወቀስ እዚያ አልተገኙም። ማንኛውም የምናገሩት ነገር አያደነግጠንም ወይም እፍረት አያሰማንም፣ ነገር ግን በተሻለ ሁኔታ እርስዎን መመርመር፣ ማከም እና መደገፍ እንድንችል ሀቁን መናገር ይኖርብዎታል። የምትናገሩት ሁሉም ነገር በኤሌክትሮኒክ መዝገብ ሥርዓታችን ላይ በሚስጥር ይያዛል፣ ወደ ሌላ አገልግሎት እርስዎን ለመላክ፣ በእርስዎ ፈቃድ፣ መረጃ ማጋራት ካስፈለገን በስተቀር። በጣም አልፈው አልፈው በሚታዩ ሁኔታዎች ውስጥ፣ ሠራተኞች ለእርስዎ ጥበቃ ሲባል መረጃ ማጋራት ሊያስገልጋቸው ይችላል።
የሚመርጡ ከሆነ፣ ወንድ ወይም ሴት የጤና ባለሙያን ለማየት መምረጥ ይችላሉ፣ ነገር ግን ክሊኒኩ ሥራ የሚበዛበት ከሆነ ከተለመደው በላይ ረጅም ጊዜ መጠበቅ ሊኖርብዎት ይችላል፣ እና ቀጠሮዎን ሲይዙ ይህንን ሊያሳውቁን ይገባል።
ለማንኛውም ፖዘቲቭ ለሆሉ በወሲባዊ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች ውጤቶች ህክምናን እንዴት አገኛለሁ?
ከSTI ውጤቶችዎ አንዱ ፖዘቲቭ እንደሆነ እና ህክምና እንደሚያስፈልግዎ ከተነገረዎት፣ ለዚህ ህክምና እንዲመለሱ አገልግሎቱ ቀጠሮ ያመቻችልዎታል።
ከመምጣትዎ በፊት ምን ይጠበቃሉ?
የቀጠሮ ርዝመቶች ከ10 ደቂቃዎች ለምርመራ ብቻ ጉብኝት እስከ 90 ደቂቃዎች ለሙሉ የምርመራዎች፣ በሽታ ምርመራዎች እና ህክምና ቅንብር ሊለያዩ ይችላሉ። በቀጠሮዎ ላይ ለፍላጎቶችዎ እንደምንጨቅ ለማረጋገጥ የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን፣ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ፣ እንደምንሰጠው የአገልግሎት አካል፣ ለሌላ ቀጠሮ ተመልሰው እንዲመጡ ልንጠይቅዎ እንችላለን።
ከቀጠሮዎ በፊት ደብዳቤ ከላክንልዎት የሚፈልጉትን ሁሉም ተገቢ የቅድመ-ቀጠሮ መረጃን እናካትታለን።
ቀጠሮ ላይ ሲገኙ ምን ይጠብቃሉ?
ለአስተርጓሚ ጠይቀው ከሆነ፣ በቀጠሮዎ ጊዜ ያገኙዎታል።
እኔ ሲደርስ ምን ይፈጠራል?
ሲደርሱ፣ የቁጥር ካርድ፣ የሚቀርበው አገልግሎት ላይ መረጃ ያካተተ ጥቅል፣ የግል መረጃዎ ምን እንደሚሆን የሚያብራራ የሚስጥራዊነት ሰነድ፣ እና የምዝገባ ቅጽ በሚሰጥዎ/በምትሰጥዎ እንግዳ ተቀባይ ይቀበላሉ። የእንግዳ ተቀባዩ/ዋ ለመመዝገብ ተራዎ እስኪደርስ ድረስ እንዲቀመጡ ይጠይቅዎታል/ትጠይቅዎታለች። የምዝገባ ቅጽ መሙላት ላይ እርዳታ የሚፈልጉ ከሆነ ለእንግዳይ ተቀባይ ማሳወቅ ይችላሉ። እባክዎ ይህንን በቻሉት መጠን ይሙሉ።
ለምን ያህል ጊዜ መጠበቅ አለብኝ?
በተሰጠዎት የቀጠሮ ጊዜ ተቀራራቢ ላይ እንዲታዩ የተቻለንን ሁሉ እናደርጋለን። እንዳለመታደል ሆኖ፣ ያ ሳይሆን የሚቀርባቸው ሁኔታዎች አሉ። ለቀጠሮ መጥተው ለ30 ደቂቃዎች ጠብቀው እና ካልተጠሩ፣ እባክዎ ለእርስዎ ምን እየተደረገ እንደሆነ መጠየቅ ለሚችል/ለምትችል የእንግዳ መቀበያ አባል ያሳውቁ። በአንድ ጊዜ የሚሰሩ ብዙ ክሊኒኮች ስላሉን፣ ከእርስዎ ኋላ የደረሰ ሰው በኋላ ሊጠሩ ይችላሉ።
ዘግይቼ ከደረስኩስ?
ታካሚዎች ለቀጠሯቸው ዘግይተው የሚደርሱባቸው አጋጣሚዎች እንዳሉ እናውቃለን። ለቀጠሮዎ ዘግይተው ከደረሱ፣ ሙሉ የመጀመሪያው የቀጠሮዎ ጊዜን ማክበር እንደምንችል ዋስትና መስጠት አንችልም። ለቀጠሮዎ ዘግይተው ሲደርሱ፣ የክሊኒክ ቡድን አባል መጥቶ/ታ እንዲያናግርዎ/እንድታናግርዎ እንግዳ ተቀባዩ/ዋ ያመቻቻል/ታመቻቻለች። አንድ ሰው እስኪገኝ ድረስ መጠበቅ ሊኖርብዎት ይችላል። ለአንዳንድ ክሊኒኮች እና አሰራሮች ከዘገዩ እርስዎን ለማየት አንችልም። ይህ የሚሆን ከሆነ፣ አማራጭ ቀጠሮን እናመቻችልዎታለን።
በማማከሪያው ጊዜ ማንን አገኛለሁ?
ብዙ አገልግሎቶቻችን የክሊኒካል ባለሙያዎች ቡድን ሠራተኞች አላቸው፣ በአገልግሎቱ መሰረት፣ ሀኪሞች፣ ነርሶች፣ የጤና እንክብካቤ እርዳታ ሰጪዎች፣ አማካሪዎች ወይም የስነ-ልቦና ባለሙያዎች ሊሆኑ የምችሉትን። ሁሉም ሠራተኞቻችን፣ እርስዎ ወደ ክሊኒክ ክፍል ሲጠሩ፣ እራሳቸውብ ያስተዋውቃሉ።
ለተለየ የክሊኒክ/የህክምና ባለሙያ ጾታ ምርጫ ካለዎት፣ እባክዎ ቀጠሮዎን ሲይዙ ያሳውቁን። ስንችል ያንን ጥያቄ ለማክበር እንሞክራለን ነገር ግን ዋስትና መስጠት አንችልም።
ምርመራዎቼ እንዴት ይወሰዳሉ?
የሽንት ወይም የደም ናሙና ማቅረብ ሊኖርብዎት ይችላል። አንዳንድ ምርመራዎች ከመራቢያ ብልቶችዎ የፈሳሽ ጥርግ እንዲወሰድ ሊያስፈልጉ ይችላሉ እና፣ ምን ዓይነት ወሲብ እንደፈጸሙ ላይ በመመርኮዝ፣ ከጉሮሮዎ እና ከትልቁ አንጀት ጫፍ (ፈንጢጣ) ሊወሰድ ይችላል። ይህ ትንሽ ምቹ ላይሆን ይችላል፣ ነገር ግን የክሊኒክ ሠራተኞች እነዚህን ምርመራዎች ለማድረግ የላቀ ስልጠና አላቸው እና በጥሩ እጆች ውስጥ ነው ያሉት። አንዳንድ ምርመራዎች ሀኪሙ/ሟ ብልቶችዎን እንዲያይ/እንድታይ ሊያስፈልጉ ይችላሉ። ተመሳሳይ ጾታ ባለው/ላት ሀኪም መታየት የተሻለ ምቾት የሚሰጥዎ ከሆነ፣ እባክዎ ቀጠሮዎን ሲይይዙ ያሳውቁን።
ልጆችን ይዤ መምጣት እችላለሁ?
ልጆችን ይዞ አለመምጣት በጣም ጥሩ ነው እናም በህንጻው ላይ የልጅ እንክብካቤ አገልግሎቶች የሉም። ከልጅዎ ጋር መምጣት ካለብዎት፣ እርስዎ በክሊኒክ ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ በመጠባበቂያ አካባቢ ውስጥ የሚያንከባክቧቸውን ሌላ አዋቂ ይዘው ኑ። ካልሆነ፣ ልጆችዎን ትተው ሌላ ጊዜ ተመልሰው እንዲመጡ ሊጠየቁ ይችላሉ።
ልጆችዎን ከሚታመን አዋቂ ሰው ጋር መተው ከቻሉ በርካታ የመጫወቻ አካባቢ ያለው ተወዳጅ ፓርክ በመንገዱ አልፎ አለ።