እኛ በታላቁ ግላስጎው እና ክላይድ አካባቢ ለሚኖሩ ሰዎች ልዩ የሆነ የወሲባዊ ጤና አገልግሎት የምንሰጥ ነን። እኛ የስኮትላንድ ብሔራዊ የጤና አገልግሎት አካል ነን። ሁሉም አገልግሎቶቻችን እና ህክምናዎቻችን በነፃ የሚሰጡ ናቸው። እንደዚሁም ምስጢራዊ እና ግላዊ ናቸው።
ተግባቢ የሆኑ ሠራተኞቻችን ሰሚ-አዕምሮ ያላቸው ሲሆኑ በፍጹም አይፈርዱብዎትም።
እርስዎ የሚከተሉት ሁኔታዎች ውስጥ ካሉ፣ እኛ በሳንዲፎርድ እርስዎን መርዳት እንችላለን፥
በሳንዲፎርድ የምንሰጣቸው አገልግሎቶች
አገልግሎቶቻችንን እንዴት እንደሚያገኙ
አገልግሎቶቻችንን ለማግኘት በቀጥታ ወደ የማካተት ቡድናችን 0141 211 8610 ላይ መደወል ይችላሉ። ብዙውን ጊዜ ከነርሶቻችን ከአንዱ/ዷ ጋር ይነጋገራሉ እና በጣም የተሻለ ቀጠሮ እንይዝልዎታለን። በዚህ ላይ እንዲረዱ የስልክ አስተርጓሚዎችን ማዘጋጀት እንችላለን ።
እባክዎ በአሁኑ ጊዜ በኮቪድ 19 ምክንያት ቀጠሮ ያላቸው ሰዎች ብቻ ወደ ሳንዲፎርድ መምጣት እንደሚችሉ ያስተውሉ።
ከታች ካሉት ክሊኒኮች ወደ አንዱ ለመምጣት መምረጥ ይችላሉ
Sandyford Central, 2-6 Sandyford Place, Glasgow G3 7NB
Sandyford Paisley
1st Floor New Sneddon Street Clinic 8 New Sneddon Street, Glasgow
PA3 2AD
Sandyford Parkhead
መግቢያ በኒስቤት መንገድ ላይ የሚገኘው ህንፃ ጎን ላይ ነው
Parkhead Health Centre 101 Salamanca Street Glasgow
G31 5BA